Monthly Archives: ሚያዝያ 2013

ግንባር፣ ትስስረ-ትውልድ እና የኢትዮጵያ ስነ-አስተዳደር

ባሁኑ ሰዓት እያንዳንዷን በግል የምትነካንን ጉዳይ ብቻ አንጠልጥለን በየቦታችን ከሮጥን፤ በመካከላችን ያለውን መቀራረቢያ ክሮች እንዲበጠሱ እያከረርን፣ በተናጠል እያደርን እየቀጨጭንና ሕዝቡንም በተስፋ አስቆራጭ መንገድ እየመራን፤ የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት እድሜ ማራዘም ብቻ ነው ሂደታችን። ከዚህ መውጣት አለብን። አዎ የአማራው ጉዳይ ከባድና አደገኛ ነው። ይኼን ለአማሮች ብቻ አንተወውም። የእስልምና ተከታዮች ጉዳይ ከባድ ነው። ይኼን ለእስላሞች ብቻ አንተወውም። የቤንሻንጉል፣ የደቡብና የኦሮሚያ ለም መሬቶች ለውጭ ሀገርና የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አባላት በርካሽ መሠጠቱ ለነኚህ አካባቢዎች ነዋሪዎች ብቻ አንተወውም። የድንበሩን ለሱዳን መሠጠት ጉዳይ ለደንበሩ ነዋሪዎች ብቻ አንተወውም። በየቦታው የኢትዮጵያዊያ ነፃ ጋዜጠኞችን መጎሳቆል ለቤተሰቦቻቸው ብቻ አንተወውም። ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች በሆነ ባልሆነው መበዝበዛቸውን ለነሱ ብቻ አንተወውም። በገፍ የኦሮሞ ልጆች መታሠራቸውን ለኦሮሞዎች ብቻ አንተወውም። ኢትዮጵያዊያን እንዲሰደዱ ለመገዳድቸው፤ ለተሰዳዶች ብቻ አንተወውም። ሀገራቸው ተመልሰው እንዳይገቡ በውጭ የሚኖሩትን ኢትዮጵያዊያ ጉዳይ ለተሰደዱት ብቻ አንተወውም። ይህ ሁሉ የሁላችን ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ነው። ይህን በአንድነት የኔ ብለን መነሳት አለብን። የዚህ ሁሉ ተጠያቂው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ነው። ይኼ ቡድን መወገድ አለበት። ይኼ ቡድን ከነስነ-አስተዳደር ፍልስፍናውና የአስተዳደር መመሪያው መወገድ አለበት። እናም ይህን ማስወገድ የሁላችን የአንድነት ግዴታ ነው። ኢትዮጵያዊ ሆነን መቆጠር አለብን። ኢትዮጵያዊ ሆነን ብቻ ነው ይኼን ልናደርግ የምንችለው። ዛሬ በውጭ ሀገር መረቡን ዘርግቶ፤ በያለንበት የመከፋፈል እኩይ ተግባሩን ለማከናወን ክንዱን እያረዘመ ነው። እስከመቼ እንጠብቃለን? Continue reading

Posted in አስተያየቶች - Commentaries | አስተያየት ያስቀምጡ

ባሁኑ ሰዓት በአማራው ወገናችን ላይ እየደረሰ ያለው አማራን የማጥፋት ሴራ፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የሚካሄደው ተግባር ዋናው አካል ነው። ክፍል ፫

ESKEMECHE No 103 አማራው ያለበትን ዕለታዊ የስቃይ ሁኔታ፣ ለምን ይህ በአማራው ላይ እየተፈፀመ መሆኑንና ለምን ይኼን የስቃይ ሁኔታ የወገን ማጥፋት ወንጀል እንዳልነው ባለፉት ሁለት ተከታታይ ዕትሞቻችን ዘርዝረናል። በዚህ የዛሬው እስከመቼ እትማችን ደግሞ፤ ለዚህ መፍትሔ በማሰብ ምን መደረግ አለበት የሚለውን እንጠቁማለን። … Continue reading

Posted in እስከመቼ - ESKEMECHE | አስተያየት ያስቀምጡ