የጉልበት ወረራ፣ የሰብዓዊ መብቶች ገፈፋና ድምጽ የለሽ ዘር ማጥፋት፤ የወልቃይት ጠገዴ የማንነትና የመልክዓ ምድር ተሐድሶ ጥረት፤ ጎንደር፤ አማራ፤ ኢትዮጵያ

የጉልበት ወረራ፣ የሰብዓዊ መብቶች ገፈፋና ድምጽ የለሽ ዘር ማጥፋት፤ የወልቃይት ጠገዴ የማንነትና የመልክዓ ምድር ተሐድሶ ጥረት፤ ጎንደር፤ አማራ፤ ኢትዮጵያ

በአቻምየለህ ታምሩ

( ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ አንዱዓለም ተፈራ እንደተረጎመው )

፩.     መግቢያ፤

የኢትዮጵያ ታሪክ፤ በሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር በመጡ ምሁራን፤ ለረጅም ዘመናት ተጠንቷል፤ ተጽፏል። ከጸሐፊዎች መካከል ከፊሎቹ ሙያተኛ ሊቆች ሲሆኑ፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ሀገር ጎብኚዎች ሆነው፤ የሄዱባቸውን ቦታዎች፣ የጉዟቸውን ውጣ ወረድና ገጠመኞቻቸውን የዘገቡ ናቸው። እኒህ ጸሐፊዎች፤ የአስተዳደር ደንበሮችን፣ ቋንቋዎችን፣ ባህሎችን፣ ወጎችን፣ እምነቶችንና ሌሎች ኢትዮጵያዊ ባህርያትን በዝርዝር አስፍረዋል። እኒህ እቅጩን ያሰፈሩ ታሪካዊ ዘገባዎች፤ በተለይ ለሰሜን ኢትዮጵያ፤ የእውነት ማስረጃዎች ናቸው። እኒህ የታሪክ ማስረጃዎች፤ በተለያዩ የአውሮፓዊያን ቋንቋዎችና፤ በሀገር ውስጥ ደግሞ በግዕዝና በአማርኛ የተጻፉ መሆናቸውን በጥሞና ልብ ማለቱ ወሳኝ ነው።

ከ፲ ፭ ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጸሐፊዎች በመተንተን ከተገለጹት ቦታዎች አንዱ፤ በሀገራችን በኢትዮጵያ አራተኛው ትልቅ ወንዝ በሆነው በተከዜ ወንዝ ወዲያና ወዲህ ያሉት ቦታዎችና በኒሁ ቦታዎች የሚኖሩትን ኢትዮጵያዊያን ነው። ከነዚህ ቦታዎች ደመቅ ያለ ዕውቅና ካገኙት አንዱ የሆነው፤ ብሎም የዚህ ጽሑፍ ትኩረት፤ በታሪካዊቷ ጎንደር፤ኢትዮጵያ፣ ያለው የወልቃይት ጠገዴ አካባቢና በዚያ ሰፍረው የሚገኙት ነዋሪዎች ናቸው። ከ ፲ ፬ ፻ ፳ ፮ ዓመተ ምህረት ጀምሮ እስከ ፲ ፱ ፻  ፹ ፫ ዓመተ ምህረት ድረስ ባለው ዘመን ያሉ ታሪካዊ ማስረጃዎችና የብራናም ሆነ የዘገባ ጽሑፎች የሚያመለክቱት፤ ወልቃይት-ጠገዴ በአማርኛ ተናጋሪው የጎንደር ክፍለ ሀገር አካል መሆኑን ነው። ይህን እውነታ የሚያረጋግጥ የማይናጋ ማስረጃ ተከማችቶ እያለ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ( ህወሓት )፤ በ ፲ ፱ ፻ ፹ ፫ ዓመተ ምህረት በመውረር፤ ወደ ታሪካዊቷ ትግራይ አጠቃሏል። በሌላ አነጋገር፤ በዛሬው የኢትዮጵያ እውነታ፤ በአማራው ፌዴራላዊ ግዛት ያለ አንድ አካባቢ፤ በጉልበት ወደ ትግራይ ፌዴራላዊ ግዛት ተዘዋውሯል። በትክክል፤ በርሃ በነበረበት ወቅት፤ በ ፲ ፱ ፻ ፸ ፪ ዓመተ ምህረት ነበር፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ወልቃይት ጠገዴ ገብቶ ቦታውን የመጪው “ታላቋ ትግራይ” አካል ብሎ  ወልቃይት ጠገዴ ገብቶ ቦታውን የመጪው “ታላቋ ትግራይ ሩፕብሊክ” አካል ብሎ ያወጀው።

በሌላ አነጋገር፤ በዛሬው የኢትዮጵያ እውነታ ሲታይ፤ በአማራው ፌዴራላዊ ግዛት ያለ አንድ አካባቢ፤ በጉልበት ወደ ትግራይ ፌዴራላዊ ግዛት ተዘዋውሯል። በወረራው ሂደት፤ የወልቃይት-ጠገዴ ታሪክ፣ ማንነትና ባህላዊ ስነልቦና ተሰልቦ፤ ተቀይሮ ተጽፎ፣ አብሶም ድራሹ እንዲጠፋ ተዘምቶበታል። ይህ ታሪካዊ ግፍ፤ በወልቃይት-ጠገዴ ላይ ለአራት አስርታት ለሚጠጋ ዓመታት ሲወርድበት ኖሯል። ይህ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ገና ሽምቅ ውጊያውን ከጥንስሱ ሲጀምር አካባቢውን ለመቆጣጠር የያዘው ኃያል ቅንብሩ ነው።

፪.     የታሪኩ መሠረታዊ አነሳስና አሁን ያለንበት ደረጃ፤

ቀሪውን የሚከተለውን ሐረግ በመጠቆም ያንብቡት —> ቀጣዩ እነሆ

አስተያየት ያስቀምጡ