የሶርያና የኢትዮጵያ ሕዝባዊ መነሳሳት፤ ተመሳሳይነትና ልዩነት ( ክፍል ፩ )

የሶርያና የኢትዮጵያ ሕዝባዊ መነሳሳት፤ ተመሳሳይነትና ልዩነት  ( ክፍል ፩ )
አንዱዓለም ተፈራ፤ የእስከመቼ አዘጋጅ

( በፒዲኤፍ ለማንበብ ይሄን ይጫኑ – – – >  ሶሪያ እና ኢትዮጵያ )

በቱኑሲያ፣ በግብጽ፣ በየመን፣ በሊቢያና በባህሬን የተከሰተውን የአረብ ጸደይ ተከትሎ፤ ሶሪያውያን ለአመጽ ሲነሱ፤ ሀገራቸው የተመሰቃቀለ ታሪክና ኅብረተሰባዊ ትስስር ስለነበራት፤ ትግላቸው መራራ፣ የከፋና ጊዜ የሚወስድ መሆኑን በመገንዘብ፤ ቀሰስ ብለው ነበር የተነሱት። እውነትም እንዳሰቡት ሆነና፤ አሁንም ትግላቸው እያዘገመ፤ የሚከፍሉት መስዋዕት እየበዛ፤ የድል ቀኑም እየረዘመ ነው። ለአራት አስርታት ዓመታት ከአባትየው ሃፌዝ አል-አሳድ ጀምሮ፤ አምባገነናዊ አገዛዝ ያዘነበባቸው አረመኔ ግፍ ስላንገሸገሻቸው፤ ከውጪ ይመጣልናል ያሉት እርዳታ ድምጹን ቢያጠፋም፤ ትግላቸው የበለጠ መረረ እንጂ፤ ለልጅየው ለበሽር አል-አሳድ አልተነበረከኩለትም። በርግጥ በውጪ ኃያላን ሀገሮች ያለው ጣልቃ ገብነትና በሃይማኖት ስበብ የሚደረገው የመካከለኛው ምሥራቅ የፖለቲካ ምስቅልቅል፤ የአንድነት ትግል እንዳያካሂዱና ትግላቸው ለድል እንዳይበቃ ታላቅ እንቅፋት ሆኗል። ባሁን ሰዓት፤ ሀገራቸው፤ የሶሪያ ሕዝብ ሳትሆን፤ የኃያላን መንግሥታትና፤ የለዘብተኛና አክራሪ ሃይማኖት ተከታዮች የጦር ሜዳ ሆናለች። ባገራችን ኢትዮጵያ ሕዝቡ ለለውጥ ተነስቷል።

በኢትዮጵያችን እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ ንቅናቄ፤ በአረብ ጸደይ ከተከሰተው ቀልጣፋ የመንግሥት ለውጥ ይልቅ፤ እንደሶርያ የተጓተተ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። ይሄ በሶርያ እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ ንቅናቄ፤ በኛ ሀገር እየተደረገ ካለው ሕዝባዊ ንቅናቄ ጋር ምን ዝምድና አለው? ምንስ ትምህርት እንወስዳለን? ይህ ነው የዚህ ጦማር ይዘት። በዚች አጭር ጦማር የሁለቱን ሀገሮች ታሪክና የትግል ሂደት በዝርዝር ማቅረብ ችግር ነው። ሆኖም ግን ጠቅለል ባለ ሁኔታ፣ የሁለቱን ሀገሮች ሕዝብና የአስተዳደር ታሪክ የግልምጫ ዕይታ በመንተራስ፣ የአካባቢውን የፖለቲካ ሀቅ፣ አሁን ያሉት አረመኔ ገዥዎች የመጡባቸው አካባቢዎች እውነታዎች፣ የአላዋይቶችና የትግሬዎች ገዥዎች እምነት፣ ዕቅድና ተግባር፣ የሕዝባዊ መነሳሳቶቹ ምክንያቶች፣ በትግሉ ዙሪያ የተሰማሩት ታጋዮች ሁኔታ፣ የያዟቸውን ትግሎችና የውጪ ኃያላን መንግሥታትን ሚና አቀርባለሁ። እናም በሁለቱ ሀገሮችና ትግሎች መካከል ያለውን ተመሳሳይነት አሳያለሁ።

ከሁሉ አስቀድሜ ግልጽ የማደርገው ጉዳይ አለ። በሀገራችን በኢትዮጵያ፤ ለሃያ አምስት ዓመታት ሲሰበክ፣ በጉልበት ሲተገበርና መንግሥታዊ መዋቅሩ ሁሉ አስተናጋጁ ሆኖ ሲንበረከክለት የነበረው፤ በትውልድ ሐረግና በቋንቋ የተመሠረተ የፖለቲካ ሥርዓት፤ እንዲሁ በቀላሉ ይቅር ወይም ይኑር በማለት የሚከላና የምንቀበለው ኅብረተሰባዊ ክንውን አይደለም። ሥር አለው። ሽታ አለው። እንደምታ አለው። ለምጥ አለው። ቅሪት አለው። ግማት አለው። ድምጽ አለው። አየሩን ሁሉ በክሏል። ሰማዩን ሁሉ አጥቁሯል። መሬቷን ሁሉ ሰርስሯል። ይህን ንቆ፤ በደፈናው ትግሬዎችን አትንኩ፤ ዝም ብላችሁ የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር ብቻ ተቃወሙ የሚለው አይሠራም። የዚህ ሥርዓት መሠረቱና አምዱ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ሆኖ፤ ግድግዳና ጣራው በዙሪያው የተኮለኮሉት ተጠቃሚዎቹ ናቸው። እኒህ ደግሞ ከዘጠና ከመቶው በላይ ትግሬዎቹ ሲሆኑ፤ ሆዳም ግለሰቦች ከሌሎችም አሉበት። ይህን ግን በትውልድ ደረጃ በተመሠረተ ያቀፉት፤ ትግሬዎቹ ናቸው። መገንዘብ ያለብን፤ በትክክል ለግለሰብ ኢትዮጵያዊነትን ማዕከላዊነት ስንቆም፤ እያንዳንዱና እያንዳንዷ ትግሬ፤ እንደሌላው ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያዊት ሁሉ፤ እኩል መብት አላቸው ብለን ነው። ነገር ግን፤ አሁን ባለው ተጨባጭ ሀቅ፤ ይሄ አኩልነት ቦታ የለውም። ስለዚህ፤ የጎበጠን ለማቃናት፤ ጎባጣውን ወደሚቀናበት ሲለመጥ፤ አልፎ መሄድና የበለጠ መጉበጡ፤ የመስተካከሉ ግዴታ ነው። ይህ በግለሰብ ደረጃ እኔ ስለወደድኩት ወይንም ስለጠላሁት የሚመጣ ወይንም የሚወገድ ሳይሆን፤ የተፈጥሮ ግዴታ ነው። እርቅ አድራጊ ሽማግሌዎች፤ ገዳዩን ይገደል ባይሉም እንኳ፤ ለጉዳቱ ተመጣጣኝ ካሣ እንዲከፍል አድርገው ነው እርቅ የሚያወርዱት። እናም ይህ ግንዛቤ ቦታ እንዲይዝ እፈልጋለሁ።

አምባገነኖች የትም ሀገር ተከሰቱ የትም፤ ባህሪያቸው አንድ ነው። ከሕዝብ አይማሩም። አዋቂዎችን ይጠላሉ። ለሁሉም አዋቂ እኛ ነን ይላሉ። ሁሉም ነገር በቁጥጥራቸው ሥር እንዲሆን ይፈልጋሉ። አንዲትም ቅንጣት ተቃውሞ አይወዱም። በጉልበት ሁሉ ነገር ይፈታል ብለው ያምናሉ። ፈረንሳይ በ፲ ፱ ፻ ፲ ፫ ሶሪያን ወርራ፤ በሚያዝያ ፲ ፱ ፻ ፴ ፰ ዓመተ ምህረት ለቀቀች። ከዚያ በኋላ፤ በተከታታይ የመንግሥት ግልበጣዎችና የበዓዝ ፓርቲ መግነን አለፈና፤ ሃፌዝ አል-አሳድ የራሱን መንግሥት ግልበጣ አድርጎ፤ ተደላድሎ የተዘረፈጠበት ዘመን ተከተለ። ምን ጊዜም በጠመንጃ ጉልበት ሥልጣንን በማራዘም በኩል፤ ሶሪያና ኢትዮጵያ አንድነት አላቸው። የትግሬዎች መንግሥትም በሥልጣን ላይ ለመውጣት የበቃው በጠመንጃ ጉልበቱ ነው። ፈሪው መንግሥቱ ኃይለማርያም፤ ሀገር ወዳዱንና ግምባር ቀደም ታጋይ ወጣቱን ፈጅቶ፤ ምሁራንን አጥፍቶ፣ ሀገሪቱን ባዶ አስቀርቶ ክፍት ቦታ ጥሎላቸው፤ ጅራቷን ቆልፋ እንደምትሾልክ ውሻ ሸውዶ ስለጠፋ፤ ሰተት ብለው አዲስ አበባ ገቡ። እነሱም እሱን አጣጥለው፤ ነገር ግን እሱኑ ሆነው መግዛት ቀጠሉ። በጠመንጃቸው ወንበራቸውን ጠበቁ። ከቻልክ ሂድና እንደኛ ተዋግተህ ወንበሩን አስለቅቀን። መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ፤ አሉት ሕዝቡን።

በ፲ ፱ ዓመተ ምህረት፤ የሶሪያ ሕዝብ ከቅኝ ገዥዋ ፈረንሳይ ነፃነቱን ለማግኘት ሲሯሯጥ፤ የበሺር አል-አሳድ አያት፤ የሃፌዝ አል-አሳድ አባት፤ ሱላይማን አሊ አል-አሳድና ፹ ( ሰማንያ ) አላዊቶች ጓደኞቹ፤ ከሶሪያ ጋር መቀላቀል አንፈልግም፤ በፈንሳይ ሥር ቅኝ ተገዢ ሆነን መቀጠል ይሻለናል ብለው፤ ፊርማ አሰባስበው ነበር። ፈረንሳይ ግን ከሱኒዎች ጋር በመሆን፤ አቤቱታቸውን ውድቅ አደረገችው። የመለስ ዜናዊ አያት አቶ አስረስ፤ ከጣሊያኖች ጋር በማበር፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንድትወረርና ፋሽስቱ ጣሊያን እግር እንዲሰድ ቀንደኛ አጋዥ ነበሩ። ( ባንዳው አቶ አስረስ ተሰማ ከቅኝ ገዥዎች ገር በመሆን ኢትዮጵያዊያን አርበኞችን ተከታትሎ የወጋ –ፎቶግራፉን ለትዝብት ይመልከቱ )።basha-asres-tessema እስኪ ባጠቃላይ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን ዝምድን ጠለቅ አድርገን እንመልከት። የፈረንሳይን ቅኝ ገዥነትና የበሽር አል-አሳድ ትውልዳዊ ከሃዲነቱንና የአሁን አረመኔነቱን ከተነሳ ዘንዳ፤ ሌሎች ተመሳሳይ ሁኔታዊችን ደግሞ እናጣቅስ። ፈረንሳይ ከአናሳ ወገኖች ወታደሮችን በመመልመል አረመኔያዊ ተግባር በሀገሩ ሕዝብ ላይ እንዲያወርዱበት አድርገለች። ለዚህም አላዋይቶች በብዛት በሠራዊቱ ነበሩ። በቅኝ ገዥዋ ትዕዛዝም፤ ብዙ በደል በሱኒዎች ላይ አዝንበዋል። በተመሳሳይ መልኩ፤ ፋሽስት ጣሊያን፤ አስካሪሶችን ከኤርትራና ከትግራይ መልምለው በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያደረሱትን፤ ታሪክ መዝግቦታል። በተጨማሪም፤ አርበኞች አያቶቻችን በትግራይ ምድር ጣሊያንን ሲዋጉ፤ ምግብ በመደበቅ፤ ከጣሊያን ዘመናዊ መሳሪያዎችን በመቀበል፤ የድብቅ ተዋጊ ሆነው ያደረሱት በደል ግልጽ ነው። አሁንም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ አረመኔያዊ ተግባራቸውን በማውረድ ላይ ያሉት፤ ከትግራይ የተመለመሉ የአጋዚ ሠራዊት እንሰሶች ናቸው።

ፈረንሳይ ሶሪያን በቋንቋ ክልሎችን መስርታ፤ የርስ በርስ ግንኙነት እንዳይኖርና ሕዝቡ በአንድነት ተባብሮ እንዳይነሳ ጣረች። syriaያኔ ፈረንሳይ አላዋይት የሚል ክፍለ ሀገር ፈጠረች፤ ጣሊያን ኤርትራን እንደፈጠረች።ethiopia ጣሊያን በኢትዮጵያ በተመሳሳይ መልኩ ይሄንኑ በቋንቋ የተመሰረተ የአስተዳደር አከላለል፤ ሳይሳካለት ባጭር ተቀጨባት እንጂ፤ አድርጋ ነበር። ከዚሁ ከቅኝ ገዥ መምህራቸው የወሰዱትን ሕዝብ የመከፋፈል አባዜ፤ እኒህ ጠባብ አረመኔዎች ተግብረውታል። ዛሬ በኢትዮጵያ ያሉት የክልል አስተዳደር ክፍፍሎች በቋንቋ የተመሰረተ ነው። ፈረንሳይ፤ የአላዊ፣ የደማስቆ፣ የጀባል፣ የአል ድሩዝ፣ የአሌፖ፣ የታላቋ ሌባነንን ከፍለ ሀገሮች መሰረተች። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ደግሞ፤ የትግሬ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የአፋር፣ የደቡብ፣ የሶማሌ፣ የቤንሻንጉል፣ የጋምቤላ፣ የአዲስ አበባና የሐረር ክፍለ ሀገሮችን መሰርታለች።

ሌላው ተመሳሳይ ነገር ደግሞ፤ በአላዋይቶችና በትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን ላይ ቅኝ ገዢዎች ያደረጉት የመከፋፋል ዕጣ ነው። ፈረንሳይ ስትለቅ፤ አላዋይቶች ያሉበትን ሰሜናዊ ክፍል ( ሃታይ ) ለቱርክ ሠጥታ ሄደች። ኢትዮጵያ ውስጥም ጣሊያን ቋሚ የሆነ ክፍፍል በትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን መካከል እንዲኖር፤ በኤርትራና በትግራይ ውስጥ ትግርኛ ተናጋሪዎችን ከፋፍላ ሄደች።

al_assad_familyበተጨማሪ፤ በ፲ ፱ ፻ ፶ ፮ ዓመተ ምህረት መጣት መኮነኖች የመንግሥት %e1%89%a3%e1%88%8d%e1%8a%93-%e1%88%9a%e1%88%b5%e1%89%b1ግልበጣ አደረጉ። በዚህ ግልበጣው ሱኒዎች፣ የግሪክ ኦርቶዶክስ ተከታይ የሆኑትን በማጥፋት፤ ሃፌዝ አል-አሳድና ሳላህ ጃዲድ፤ የአላዊ መኮንኖችን ብቻ የያዘ ግልበጣ በማድረግ፤ በዓዝን አጠፉት። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ከሸዓቢያና ከኦነግ ጋር አዲስ አበባ መግባቱንና በኋላ ኦነግን መደምሰሱን ያስታውሷል። ( በፎቶግራፉ ላይ የምትመለከቱት የአፌዝ አል-አሳድ ቤተሰብ። ከቆሙት ከመሐል ያለው ሃፌዝ ይተካኛል ብሎ ያጨው ልጁ ነበር። በአደጋ ሲሞት ከሱ በቀኝ ያለው በሺር ቦታውን ወሰደና ያባቱን አረመኔ ተግባር ቀጠለበት።) (በቀኝ በኩል ያለው ደግሞ ሀገር አጥፊው ከነአጋሩ ነው።)

ሃፌዝ አል-አሳድ በ፲ ፱ ፻ ፷ ፫ ዓመተ ምህረት ሥልጣኑን ሲወስድ፤ ለጠቅላላ ሶሪያዊያን መብረቅ የመታቸው ነበር የመሰለው። ያልተጠበቀ ነበር። የፖለቲካ ብስለት፣ የድጋፍ መሰረት፣ ሆነ ችሎታ የሌለው ነው በማለት፤ ደማስቆና አብዛኛው የሶሪያ ሕዝብ እውነት አልመሰለውም ነበር። ውሻ መቅደስ ውስጥ የገባች ያህል ነበር ሕዝቡ በመገረም ደርቆ የቆመው። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አዲስ አበባ ገብቶ ሥልጣን ሲወስድ፤ ምንም እንኳ በአረመኔው መንግሥቱ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ ሕዝብ ተማሮ፤ ሰይጣን ቢመጣም ይሁንበት! የሚል ግንዛቤ ቢኖረውም፤ ውለው ያድራሉ ብሎ አልገመተም ነበር።

የአካባቢው የፖለቲካ ሁኔታ፤ ኢትዮጵያና ሶርያ፤ ለረጅም ዘመናት የሕዝብ መኖሪያ ሆነው፤ በብዙ ክፍለ ዘመናት የሚቆጠሩ የመንግሥታት ምሥረታና ሀገራዊ የርስ በርስ መዋጋቶች ታሪክ በተዘገበበት የመካከለኛው ምሥራቅ ይገኛሉ። ሶርያ በእስራዔልና በአረብ ሀገሮች መካከል ያለው መባላት በማይነጥፍበትና በመባላቱም ያፈጠጠውን ጥርስ ያገጠጠችበት እውነታ ሲውጣት፤ በውስጧ ደግሞ በተለያዩ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መካከል የማይበርድ ፍትጊያ ያልተለያት ናት። አናሳም ይሁኑ እንጂ፤ ክርስትያኖች የዚሁ ቀመር አንድ ክፍል ናቸው። የአረቦችና እስራዔል መፋጀትን በተመለከተና የተለያዩ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መባላት፤ በሶርያ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን፤ በመካከለኛው ምሥራቅ ያሉ ሀገሮች በሙሉ የተዘፈቁበት እውነታ ነው። ኢትዮጵያም ብትሆን፤ የዚሁ የመካከለኛውን ምሥራቅ እውነታ የደቡቡን ጫፍ የያዘች ስትሆን፤ በውስጧም በተመሳሳይ መልኩ የርስ በርስ መጨፋጨፉ የተመዘገበ ነው።

የሁለቱ ሀገሮች ሕዝብና የአስተዳደር ታሪክ፤ በሁለቱም ሀገሮች፤ የተለያዩ የእምነት ተከታዮች ሲኖሩ፤ ብዙ አናሳ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ያሉባቸው ናቸው። ክርስትያኖችና የእስልምና እምነት ተከታዮች በሁለቱም ሀገሮች ሲኖሩ፤ በኢትዮጵያ የክርስትና ዘርፉ የተለያዩ ቅርንጫፎች አሉ። በሶሪያ ደግሞ የተለያዩ የእስልምና ተከታይ ዘርፎች አሉ። ሶርያ ክርስትያኖችም አሉባት። በሁለቱም ሀገሮች በአንድ ቤተሰብ ዙሪያ የተውጠነጠነ የአገዛዝ ሥርዓት ነግሶ ለዘመናት የቆየ ነው። ሕዝባዊ ተኮር የሆነ አስተዳደርና በሕዝቡ ፈቃድ የተመሠረተ መንግሥት ለሁለቱም ሀገሮች ባዕድ ነው። ሶሪያ በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ውላ፤ በመጨረሻ ፈረንሳይ ስትወጣ፤ እንደማንኛውም ቅኝ ገዢ ሁሉ፤ የቅኝ ግዛቷን የወደፊት አመሰቃቅላ ትታ ሄዳለች። በኢትዮጵያ በኩል ቅኝ ግዛትነቱ ባይኖርም፤ በቅርብ ጊዜ የነበሩት ተከታታይ ገዥዎች፤ የሚከተለው ገዥ ያማረ አስተዳደር እንዳይኖረው ሀገሪቱን አመሰቃቅሎ የተወበት፣ ተከታዩ ደግሞ ራሱ የቀረጸውን የጭንቅላቱን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ፤ አዲስ ጠፍጥፎ ለመሥራት የተነሳበት ሀቅ ተከስቷል።

አሁን ያሉት ገዥዎቻቸው መነሻ አካባቢዎች እውነታዎች፣ በሶሪያ ሥልጣኑን የጨበጠው ቤተሰብ፤ ከአላዋይቶች የመጣ ነው። አላዊት በሰሜን ምዕራብ፤ ጠረፉን ይዛ የምትገኝ፤ በጣም ተራራማና የድሃዎች አካባቢ ናት። ፈረንሳይ ስትለቅ ግማሽ አካሏን ለቱርክ ሠጥታባቸዋለች። እናም በቱርክ የደቡብ ምሥራቅ ክፍል አላዋይቶች አሉ። የጠቅላላ የሶሪያ አስር እስከ አስራ አንድ በመቶ የሚሆነው ሕዝብ አላዋይት ነው። ከደማስቆ የራቁ ከመሆናቸው በላይ፤ ከተሜነትን ባለማወቃቸው፤ በሌሎች የተናቁ ነበሩ። ራሳቸውንም ማግለል ስለሚመርጡ፤ ዳረኛ ወይም ፈንጠርተኛ ተደርገው ተወስደዋል። በትግሬዎች በኩል ደግሞ ስናይ፤ በሀገራችን ሰሜን በኩል ኤርትራን አዋስነው ይገኛሉ። በጣሊያን ጣልቃ ገብነት የተነሳ፤ በደጋው የኤርትራ ክፍል ትግርኛ ተናጋሪዎች አሉ። ከአዲስ አበባም በጣም የራቁ ናቸው። የትግራይ መሬት ለዘመናት በተለምዶ የርሻ ዓይነት ስለተበላ፤ መሬቱ የተራቆተ ነው። እናም አመራረቱም ያን ያህል ነው። ስለዚህ ትግሬዎች በየቦታው ተበትነው ይገኛሉ። በወልቃይትም በሠራተኝነት በብዛት እየተመላለሱ አገልግለዋል።

(የሶርያና የኢትዮጵያ ሕዝባዊ መነሳሳት፤ ተመሳሳይነትና ልዩነት  ( ክፍል ፪ ይቀጥላል )