እስከመቼ ኢትዮጵያ!

የማይነጥፈው የኢትዮጵያ ማህፀን፤
ከዓመት ዓመት፣ ከገዢ ገዢ
ካምባገነን አምባገነን፤
ሳይደክም ሳያርፍ የሚጎርፈው፣
ሚሊዮን ሃያ ሁለት አፍርቶ ነበር በትውልዴ እኔ ሳውቀው።

አሁንማ፣    አሁንማ፣
ካራት እጥፍ በላይ አድጓል አሉኝ፤
ደስታ በፊቴ ሲረጩልኝ።
የማይደክመው መቃብር በበኩሉ፤
ቀን ነው መሽቷል
ሳይል አፉን ከፍቶ በጥቅሉ፤
ያጋፈዋል ልጆቿን በሙሉ።
እስኪ ተጠየቅ ታሪክ!
       እስኪ እንጠየቅ እኛ!    

ቀሪውን ይሄን -> እስከመቼ ኢትዮጵያ!  በመጫን ያንብቡ