Monthly Archives: ጥር 2013

በመክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ የአስተያይት ልውውጥ፤ የማውቃቸውን ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም እንዳሉ አገኘኋቸው

በመጀመሪያ የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያምን መጽሐፍ እድሉ ገጥሞኝ ያላነበብኩት መሆኑን ከወዲሁ ላሳውቅ እፈልጋለሁ። ለወደፊቱ የማንበብ እቅድ አለኝ። ይህ ጽሑፌ የሚመለከተው በአቶ ዳንዔል ክብረትና በፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም መካከል ስለተደረገው አስተያይትና ልውውጥ ነው። በመጽሐፉ ላይ ወይንም በውስጡ በተካተቱት ሃሳቦች አለመሆኑን ማሳወቅ … Continue reading

Posted in አስተያየቶች - Commentaries | 4 Comments

መጥኔ ቧሂት!

መጥኔ ቧሂት! (ቧሂት በጎንደር ክፍለ ሀገር፤ በስሜን አውራጃ፤ በጃናሞራ ወረዳ፤ ከራስ ደጀን ማዶ ለማዶ፤ በመሻህ ወንዝ ተከፍሎ የሚገኝ፤ ምንአልባትም በሀገራችን የመጨረሻው ብርዳማ ቦታ ነው።) በጥቅምቱ የብርድ ጥፍር ተፈጥርቆ በደጋው አንኳታች ውርጭ ታጭቆ ንፍጡ አፍንጫው ላይ ደርቆ፤ የግሮቹ ጣቶች የለሁም ብለው ርቀው ጣቶቹ እንደ እንጨት … Continue reading

Posted in ስነ ጽሑፍ - Literature | አስተያየት ያስቀምጡ

ቆረቆረኝ መቃብራችሁ

  ቆረቆረኝ መቃብራችሁ በየከተማው በየገጠሩ በየጥሻው በየቆንጥሩ በለጋ ሕይወታችሁ ገና ፀሐይ ሳትመታችሁ፤ “ነፃነት ነፃነት የምትሹ ተዋጉለት አትሸሹ።” እያላችሁ ቆማችሁ፤ አባራሪ ግንባር ሆናችሁ ቀንዲል ብርሃን ተነስታችሁ፤ ፀሐይዋ በዕርጋታ በሀገራችን ወጥታ ገብታ፤ ጨለማው ፈርቶ ሸሽቶ ብርሃን ባገር ሞልቶ የማይታሰበውና ደረቁ ሀቅ በውጥረትና … Continue reading

Posted in ስነ ጽሑፍ - Literature | አስተያየት ያስቀምጡ

የእግር ኳስ ቡድናችን በዛሬው ቀን

የእግር ኳስ ጨዋታ ለኢትዮጵያዊያን ከረጅም ርቀት ሩጫ ውድደር ጋር ከፍተኛ ቦታ የያዘ ነው። በእድሜያችን ገፋ ላልነው፤ የነመንግሥቱ ወርቁ የኳስ ጥበብ፤ የኢታሎና ሊቻኖ . . . ኧረ ስንቱን በትዝታ ዓለም መጎብኘት ይቻላል። ብቻ ለሁሉም ያንን እንዳስታውስ ያደረገኝ፤ በዛሬው ዕለት ከቤቴ ተቀምጨ … Continue reading

Posted in አስተያየቶች - Commentaries | አስተያየት ያስቀምጡ

የጣመ ውይይት

የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች ተቋማዊ ድክመት ወይስ የራዕይና ስትራተጂ ልዩነት? በአቶ ጋሻው አለሙ ተጀምሮ የምናደርገው ውይይት – ጥር ፮ ቀን ፳ ፻ ፭ ዓመተ ምህረት ዋናው ቁም ነገር ከሁለታችን ውጪ፤ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ቢሳተፉበትና ሀገራዊ ስፋት ብንሠጠው ነውና፤ እባካችሁ ተሳተፉ። ሁለታችን ብቻ … Continue reading

Posted in አስተያየቶች - Commentaries | አስተያየት ያስቀምጡ

ራስ ዳሸን ምን ማለት ነው?

ጥር ፪ ቀን ፳፻፭ ዓመተ ምህረት በተደጋጋሚ ሲባል ሰምቻለሁ። እንዲያው ሲገርመኝ ብቻዬን አሟገታለሁ። አሁን ግን መድፈር ብሎኛል። ራስ ዳሸን ምን ማለት ነው? እባካችሁ ንገሩኝ? ነገርን ነገር ያመጣዋልና ጨዋታዬን በራሴ ገጠመኝ ልጀምር። ሱዳን ተሰድጄ ነበር። ካርቱምና ኦምዱርማንን ለይቶ በሚያልፈው የአባይ ወንዝ … Continue reading

Posted in አስተያየቶች - Commentaries | 4 Comments

የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች ተቋማዊ ድክመት ወይስ የራዕይና ስትራተጂ ልዩነት? አቶ ጋሻው ዓለሙ

reflection-on-Ato-Andualems-comments ይኼ የአቶ ጋሻው ዓለሙ ሁለተኛው ጽሑፋቸው ነው።

Posted in አስተያየቶች - Commentaries | አስተያየት ያስቀምጡ

የወያኔ መሪዎችና ሥርዓቱ ከሥልጣን ሲወገድ ጥሎልን የሚሄደው የባህል ለምጥ

የወያኔ ሥርዓት መውደቁ አይቀሬ ብቻ ሳይሆን፤ ቀኑ እየተቃረበ ነው። ይኼን፤ በማንኛውም ወገን፤ በወያኔም ሆነ በኢትዮጵያ ሕዝብ ወገን ለተሠለፈ ኢትዮጵያዊ መንገር፤ አዲስ ዜና ማብሰር አይሆንም። ዜና የሚሆነው፤ ወያኔ ሲወገድ በሚተካው ሥርዓት፤ ወያኔ የሚተውልን ባህሪ ይቀጥላል የሚለው አመለካከቴ ነው። ወያኔ መወገድ አለበት። … Continue reading

Posted in አስተያየቶች - Commentaries | አስተያየት ያስቀምጡ

የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች የተግባር ድክመት ወይንስ የግብና እቅድ ልዩነት፤

ታህሣሥ ፳፰ ቀን ፳፻፭ ዓመተ ምህረት “የተቃዋሚፖለቲካኃይሎችበድረ–መለስኢትዮጵያ፣ርዕዩተ ዓለምና የትግል ግብና ዕቅድ ሁኔታዎች”  በሚል ርዕስ አቶ ጋሻው ዓለሙ ጥሩ የመወያያ ሃሳብ አቅርበውልናል። ማለፊያና ብዙ የምስማማባቸውን ነጥቦች የያዘ በመሆኑ፤ ላመሰግንና ድጋፌን መስጠት እፈልጋለሁ። መቼም ብዕሬን ያነሣሁ ተስማምቻለሁ ለማለት ብቻ አይደለም። የተስማማሁባቸውን መደረቱም … Continue reading

Posted in አስተያየቶች - Commentaries | አስተያየት ያስቀምጡ

የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች በድረ-መለስ ኢትዮጵያ፣ አይዲዮሎጂካል እና ስትራተጂካዊ ሁኔታዎች በጋሻው አለሙ

Opposition-Politics-in-Post-Mels-Ethiopia ይኼን ያቀረብነው፤ አቶ ጋሻው ዓለሙ ባቀረቡት ሃሳብ ተመርኩዞ የተደረገውን ውይይት ለአንባቢ ረዳት እንዲሆን በማሰብ ነው። ይሄ የመጀመሪያው ሲሆን ተከታዩ ቀጥሎ ቀርቧል።  

Posted in አስተያየቶች - Commentaries | አስተያየት ያስቀምጡ