ሕዳር ፲፭ ቀን ፳፻፮ ዓመተ ምህረት

በዛሬው ዕለት ብዙ የኢትዮጵያዊያን ድረገጾችን እየዞርኩ አነበብኩ። በአማርኛ የተጻፉትን አነበብኩ። በእንግሊዝኛ የተጻፉትን አነበብኩ። በየሄድኩባቸው ደረገጾች በሙሉ አንድ ሁሉን ጽሑፎች የሚያስተሳስር የጋራ የሆነ ክር ተገነዘብኩ። ሁሉም በግልፅ የሚጠቁሙት፤ ይህ በሳዑዲ አረቢያ የተፈፀመው በደል፤ እንደሌሎቹ በደሎች ሁሉ በሳዑዲዎች ብቻ ሳይሆን በዋናው ጠላታችን የተቀነባበረ ግፍ ነው። ካሁን በፊት የተደረገና ለወደፊትም የሚቀጥል ግፍ ነው። እናም የግፎቻችን መንስዔ የሆነውን ይኼን ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ ቡድን እስካላስወገድን ድረስ፤ ግፉ በተለያዬ መልክ ይቀጥላል። እናም አንፍቀድለት ነው።
ታዲያ ሁላችን ይኼን የምንል ከሆነ፤ ምን አገደን?
ምን አገደን?
ይኼና ይኼ ብቻ ነው በፊታችን የተደቀነው ጉዳይ።
አንዱ የተገነዘብኩት መልዕክት፤ “ለደረሰብን በደል ዋናው ተጠያቂ ወገንተኛው አምባገነን ሕገወጡ ቡድን ነው።” የሚለው ነው።
ትክክል።
ሁለተኛው ደግሞ “ሰዓቱ አሁን ነው።” የሚለው ነው።
ትክክል።
ሶስተኛው መልዕክት ደግሞ “ለየብቻችን ሆነን አይሳካልንም፤ ቢሳካም ተመልሶ ያው ትግል ነው።” የሚለው ነው።
ታዲያ ለምን በአንድ አንሠለፍም?
እንግዲህ ሌላ አስተማሪ አያስፈልገንም። እኛው ችግራችንን በደንብ ዘርዝረነዋል። እኛው መልሱን በግልፅ አስምረን አስቀምጠነዋል። አሁን የተግባር ጥሪ ነው።
እንሰባሰብ
ለሀገር ጉዳይ እንሠለፍ ሀገራችን ከሁሉም ትበልጥብናለች
የየግል አጀንዳችንን ጣል እናድርግ
ከሌሎች ተባባሪ ከሆኑን ጋር ለመተባበር ትሁት ሆነን እንቅረብ
አንድ ጥሪ! አንድ ሀገር! አንድ ትግል!
እባካችሁ !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

About አንዱዓለም ተፈራ

በዐማራው ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ፤ ለዐማራው ያለኝን ተቆርቋሪነት ወደ ላይ አጡዞት፤ የምችለውን በሙሉ ለዚህ ለተዘመተበት ዐማራ ሕልውና ለማድረግ የቆምኩ ታጋይ።
This entry was posted in አስተያየቶች - Commentaries. Bookmark the permalink.

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s