ግንባር፣ ትስስረ-ትውልድ እና የኢትዮጵያ ስነ-አስተዳደር

ግንባር፣ ትስስረ-ትውልድ እና የኢትዮጵያ ስነ-አስተዳደር የሚለውን ንባብ በዚህ አስፈንጣሪ ( ግንባር፣ ትስስረ-ትውልድ እና የኢትዮጵያ ስነ-አስተዳደር ) ያገኙታል።

ለኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ

ለኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ – ዴሞክራሲያዊ

ለግንቦት ሰባት

ለግንቦት ሰባት – ዴሞክራሲያዊ

ለኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር

ለኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ

ለሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት

ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች የጋራ እንቅስቃሴ አስተባባሪ ኮሚቴ

ለኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ

ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር

በየቦታው ላላችሁ የስነ-አስተዳደር የትግል ድርጅቶች

በየቦታው ላላችሁ የስነ-አስተዳደር የትግል መድረኮች

በየቦታው ላላችሁ ታጋይ ኢትዮጵያዊያን

በየቦታው ላላችሁ ኢትዮጵያዊ ድረ-ገፆች

በየቦታው ላላችሁ ኢትዮጵያዊ ሬዲዮና ጋዜጦች

ውድ ኢትዮጵያዊያን፤

ወደ ትክክለኛው ሕዝባዊ ግብ ለማምራት፤ በሀገራዊ ጉዳዮቻችን ላይ ሀገራዊ ውይይት ማድረግ አለብን።

የትስስረ-ትውልዱ አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ እየፈፀመ ያለው ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ምግባር ከመቼውም የበለጠ የከፋና መመለሻ የሌለበት ደረጃ ላይ ደርሷል። እናም የሀገራችንን የወደፊት ዕጣ በጣም አደጋ ላይ አስቀምጦታል።

በተቃዋሚዎች በኩል፤ ለዚህ እኩይ ተግባሩ፤ በመጨረሻ እንዲሳካለት ለሚፈልገው ሀገር የመበታተን እቅዱን የሚረዳ መልስ ሳይሆን፤ ራሱን መስቀያ ገመድ የሚሆንበትን መንገድ መፈለግ አለብን። ይኼውም ሁላችን በአንድነት አንድ መልስ በመሥጠት ለተግባር አንድነት መነሳት ነው። አንድ ሀገራዊ አስተባባሪ አካል መመሥረት አለብን።

ለዚህ ይረዳን ዘንድ በኛ በኩል የመወያያ ጽሑፍ አዘጋጅተን፤ ከዚህ ጋር አባሪ አድርገን ልከናል። መድረኩን በማዘጋጀት፣ ተሳታፊ በመሆን፣ ሃሳቡን በማሠራጨት ወይንም ፈቃደኛ በሆኑበት መንገድ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን።

እዚህ ላይ ዶክተር ተክሉ አባተ በመጋቢት ፳፯ ቀን ፳፻፭ ዓመተ ምህረት “በትስስረ-ትውልድ የተመሠረተ ስነ-አስተዳደር በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በድረ-ገፆች ባስለጠፉት ጽሑፋቸው በማጠቃለያቸው የሚከተለውን አስፍረዋል፤

ማጠቃለያ

“ትስስረ-ትውልድ የኢትዮጵያን ስነ-አስተዳደር አጥለቅልቆታል። በገዥው ፓርቲና በተቃዋሚዎች መካከል ያለ የጋራ ክር ነው። ሁለቱ ክፍሎች፤ በትክክል ከተነጋገርን፤ ከልዩነታቸው ይልቅ፤ ብዙ የሚጋሯቸው አሉዋቸው። የተለያዩ አካል ከሆኑ፤ የሥልጣንና የበላይ የመሆን ጉዳይ ላይ ብቻ ነው። በገዥው ፓርቲና በተቃዋሚዎቹ መካከል ያለው ልዩነት በጠበበ ቁጥር፤ የስነ-አስተዳደር ትግሉ የበለጠ ትርጉም የለሽና ተስፋ አስቆራጭ ይሆናል። ለዚህም ነው ሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ተስፋ ስጪ ዕድገት የማናየው። ተቃዋሚው ወገን ለኢትዮጵያ ስነ-አስተዳደርና ስለ ኢትዮጵያ አስተዳደር ተቆርቋሪነት ካለው፤ ከመሸጉበት የትስስረ-ትውልድ ጉድጓድ ውጭ ማሰብና መተግበር አለባቸው። ኢትዮጵያ፤ ከትስስረ-ትውልዶቿና ከስነ-አስተዳደር ፓርቲዎች ስብስብ በጣም ከፍ ያለችና የላቀች ናት።”

ሙሉ ለሙሉ እንጋራቸዋለን። (ያለፈቃዳቸው ከጽሑፋቸው ተርጉመንና ጠቅሰን ስለወሰድን፤ ይቅርታ እንጠይቃለን። ሁላችንም ልናነበው የሚገባ ጽሑፍ ነውና እንድታነቡት እናበረታታችኋለን። የተጻፈው በእንግሊዝኛ ነው።)

ከታላቅ አክብሮት ጋር

የእስከመቼ አዘጋጅዎች

https://nigatu.wordpress.com/

ግንባር፣ ትስስረ-ትውልድ እና የኢትዮጵያ ስነ-አስተዳደር የሚለውን ንባብ በዚህ አስፈንጣሪ ( ግንባር፣ ትስስረ-ትውልድ እና የኢትዮጵያ ስነ-አስተዳደር ) ያገኙታል።

About አንዱዓለም ተፈራ

በዐማራው ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ፤ ለዐማራው ያለኝን ተቆርቋሪነት ወደ ላይ አጡዞት፤ የምችለውን በሙሉ ለዚህ ለተዘመተበት ዐማራ ሕልውና ለማድረግ የቆምኩ ታጋይ።
This entry was posted in አስተያየቶች - Commentaries. Bookmark the permalink.

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s