ብዙዎቹ ሞተው አንዱ ተቀበረ

ብዙዎቹ ሞተው አንዱ ተቀበረ

ሺዎቹን አሳዶ – ብዙዎችን ገድሎ

ሰማንያ ሚሊዮን – ሕዝብን አጎሳቅሎ፤

 አስለቅሶ ውሎ    –     አስለቅሶ አምሽቶ    –    አስለቅሶ ሌሊት

ያለ ዕረፍት ጠዋት ማታ

          ሕዝቡን ሲያንገላታ

                   ሕዝቡ ጨልሞበት     –      ለሱ እየነጋለት፤

 የብዙዎቹ አካል      –     ተጥሎ በመና፤

        አንዱ ተቀበረ      –      ያገር ወግ ሆነና!

ቆርጦ እንደገደለን  –  በሉ እስኪ ቅበሩት

እሱም ሰው ነውና  –  በሉ ይግባ መሬት!

ኢትዮጵያ ሀገሬ ባለሚሊዮን ሕዝብ

ሚሊዮን ወገኔ    –     ነፃነትህ ጠፍቶ      –     ትንፋሽህ ሲለገብ

ልሳንህ ሲገፈፍ     –     ዓይንህ ተሸፍኖ       –      እጅ እግርህ ሲታቀብ

አወይ የተፈጥሮ   –  የሚገርመው ነገር

እንዴት ብዙው ሞቶ   –  አንድ ብቻ ይቀበር!

ምነው ሀገራችን  –  ሰው አጣች ወይ በዕርግጥ

ሚሊዎኖች ጠፍተው  –  ላንድ ሀዘን መቀመጥ?

እኔ የሚገርመኝ       –       እንዴት ሊቻለን ነው?

ላንድ እንዲህ ያለቀስን፤    –    ለሺዎቹ ምነው?

መሞታቸው ታውቆ  –  የናታቸው እንባ  –  ጠብ ላይል ሆድ ደርቆ

የልብን ግድግዳ  –  ያንጀት ውስጥ ንጣፉን  –  ፈቅፍቆ ፈቅፍቆ

                               እንዳይድን        –             ሞሽልቆ

የዘላለም ክፍተት በቀሪው ታምቆ

ኑሮን በንፉቅፉቁ ሊገፋ ታርቆ

መተንፈሻ ጠፍቶ ሀ –  ቁ ዋዛ ቀረ

ብዙዎቹ ሞተው   –  አንዱ ተቀበረ

አኝዋክ ታጨደ  –  እንደከብት ታጉሮ

ኦጋዴን ተቃጥሎ  –  ኦሮሞው ተመትሮ

አማራው ካለበት  –  ካገሩ ተባሮ

ከለመደው ቀዬ  –  በግፍ ተመንጥሮ

ላንዱ ተለቀሰ  –  የወያኔ ኑሮ

እስስት ነው ስልባቦት

          ገደል የሚከተት

ወንጀሉ ተቆጥሮ

          የሚፈረድበት?

ዴሞክራሲን ሰብኮ  –  ጭቆናን ያስፋፋ

ነፅነትን ለፎ  –  ባርነት የገፋ

እኩልነት ብሎ  –  አድልዖን ያሰፋፋ

ትብብር እያለ  –  ብቻውን ጠለፋ

ሀገርን አሳደግሁ   –   እመኑኝ እያለ

ሀገርን መቀመቅ  –   ከቶ ያማሰለ

ምን ቢደነፋብን   –   ሰው መሆኑ አልቀረ

ብዙዎችን ገድሎ   –   እሱ ተቀበረ!

በነቂስ ተቆጥሮ   –   ባዋጅ ተመንጥሮ

ሙሾ ተወርዶልህ   –    አልቃሾች ተቀጥረው

በል እንኳን ተሸኘህ   –    አንተም ሙት እንደሰው

በሉ ወገኖቼ   –   ቅበሩት ምሳችሁ

ባኖ እንዳይነሳ   –   ደንጋዩን ጭናችሁ

እርግጡት መቃብሩን   –   ባንድ ላይ ሆናችሁ!

About አንዱዓለም ተፈራ

በዐማራው ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ፤ ለዐማራው ያለኝን ተቆርቋሪነት ወደ ላይ አጡዞት፤ የምችለውን በሙሉ ለዚህ ለተዘመተበት ዐማራ ሕልውና ለማድረግ የቆምኩ ታጋይ።
This entry was posted in ስነ ጽሑፍ - Literature. Bookmark the permalink.

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s