የአማራ የሕልውና ጥሪ – ወልቃይት ክብሪታችን ነው!

የአማራ የሕልውና ጥሪ  –  ወልቃይት ክብሪታችን ነው!
እሁድ፣ ሐምሌ ፲ ቀን፤ ፳ ፻ ፰ ዓመተ ምህረት ( 7/17/2016 )
አንዱዓለም ተፈራ  –  የእስከመቼ አዘጋጅ

ለጎንደር ኅብረት ማህበር
ለጎንደር ልማት ማኅበር
ለደንበር ኮሚቴ
ለጠለምት ልጆች ማኅበር
ለወልቃይት ጉዳይ አስፈፃሚ
ለሞረሽ ወገኔ
ለቤተ አማራ ወጣቶች
በመላው ዓለም ተበታትናችሁ ለምትገኙ የአማራ ልጆች

ውድ ዘመዶቼ፤

ዘግንኖኝ ዘግንኖኝ፣ ስበግን ከርሜ
አሁን አጥር ዘለልኩ፣ ልቆጠር ነው ቆሜ።

እያንዳንዱ ድርጅት የተመሠረተበት የየራሱ የሆነ ምክንያት አለው። በየቦታቸውና በየጊዜያቸው መፈጠራቸው፤ ያነገቡት ጉዳይ አስፈላጊ መሆኑን አስምሮበታል። ይህ ተጨባጭ ሀቅ ነው። ዛሬ በጎንደር እየተካሄደ ያለው የሞትና የሽረት ትግል፤ ይሄንን የያንዳንዳችሁን የወደፊት ሂደት፤ የምንነት ጥያቄ  አቅርቦላችኋል። በጎንደር የተነሳው የአማራው የሕልውና ጥያቄ ነው። ይህን የአማራ ወገናችን፤ አማራ ነህ ወይንም አይደለህም ብሎ የነገረው፣ ያስተማረው፣ የቀሰቀሰው የለም። ይልቁንም አማራ ነኝ፣ በአማራነቴ የሚደርስብኝ ውርደት በቃ ብሎ፤ በአማራነታችን አንገታችንን እንድናቀና እኛን አስተምሮናል። የወልቃይትን የምንነት ጥያቄ፤ ወራሪው የትግሬዎች መንግሥት አይመልሰውም። ለሱም የሕልውና ጥያቄ ነው። ለኛም የሕልውና ጥያቄ ነው። እናም የመንግሥቱን ሙሉ ኃይል እንደሚያፈስብን የታወቀ ነው። በውስጥ ያሉት አማራዎች ተነስተዋል። እኛስ ምን እንላለን?

እስከዚች ወር ድረስ፤ እኔ፤ ባደግሁበት የኢትዮጵያ አንድነት ተጎፍኜ፣ በኢትዮጵያዊያን አንድ ሕዝብነት አምኜ፣ በአንድ ብሔርነቷ ተከውኜ፣ ጆሮዬን ቢቆርጡት እንኳን ካለ ኢትዮጵያ አንድነት፤ ፍጹም ሌላ አልሰማም ነበር። የትግሬዎች መንግሥት ለረጅም ጊዜ ያደረገው የዘር ፖለቲካ ሂደት፤ በሕዝባችን የፖለቲካ ግንዛቤ ጥፍሩ ዘልቆ ገብቶ ስለደነደነ፤ በተጨባጩ ሀቅ መገዛት ግድ ሆነብኝ። እየመነመነ የሄደውን የአንድ ኢትዮጵያ ምኞቴ ትግል፤ መረመርኩት። በቦታው ቀፎ ሆኖ ታዬኝ። ተማርኩ። ለሀቁ ተገዛሁ። በዚህ በወራሪው የትግሬዎች ገዢ ቡድን፤ የአማራው የሕልውና ጥያቄ፤ ከሁሉም ነገር በላይ ሆኖ በለጠብኝ። ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ፤ በመላ ኢትዮጵያ ተበታትኖ የሚኖረው የአማራው ወገኔ ብሶትና በደል፤ አሁን ከምችለው በላይ ሆነብኝ። ዘረኛው የትግሬዎች መንግሥት፤ ወሰን በሌለው እብሪት ያካሄደው የመከፋፈል ፖለቲካ፤ የማይቀለበስበት ደረጃ መድረሱ ተሰማኝ። ለአማራው የመኖር ወይንም ያለመኖር፣ የመሞት ወይንም ያለመሞት ትንቅንቅ ሲሆንበት፣ ደንበር መለየት ግድ ሆነብኝ። እናም በአማራነቴ እንድቆም፤ በጎንደር እየተካሄደ ያለው የትግሬዎች ወረራ ገዛኝ። ይህን ምርጫ በመውሰዴ ምንም ዓይነት ቅሬታ የለኝም። ይልቁንም የግዴታ ምርጫዬን ማስተካከሌ ደስታ ሠጥቶኛል። ተምሬበታለሁ።

በጎንደር እየተካሄደ ያለው፤ በትግሬዎችና በአማራዎች መካከል፤ ላጥፋህ አልጠፋም ግብግብ ነው። በቦታው አማራው፤

ሲቆርጡት እያየሁ፣ ሞፈሩን ከበሬ
ጊዜ ይፍታው ብዬ፣ አንጀቴን ቋጥሬ
መግፋት ቀኑን ብይዝ፣ ሀገሬን አክብሬ
ሰይፉን አንገቴ ላይ፣ ወደሩት ወይዛሬ!
ምርጫው እንደጠፋ፣ የታሰረ በሬ
ተገዝግዤ ልሞት፣ በወራሪ ትግሬ
በቃ አለቀ እንግዲህ፣ እሪ በይ ሀገሬ!

በማለት ተነስቷል።

ውድ በአማራው ስም የምትንቀሳቀሱ ግለሰቦችና ስብስቦች፤

እያንዳንዳችሁን ያነሳሳችሁና እንድትሯሯጡ የገፋችሁ ዋናው ምክንያት፤ የአማራው የሕልውና ጉዳይ ነው። ምንም እንኳን በአደረጃጀት ዘይቤም ሆነ በአሰራር ሂደት አንዳችሁን ከሌላችሁ የተለየ የሚያደርጋችሁ ጉዳይ ቢኖርም፤ መሠረታዊ የሆነው ዋናው ጉዳይ፤ የአማራው ሕልውና ነው። አሁን የአማራው ሕልውና በመፈተን ላይ ነው። አማራው የሚጠፋበት ወይንም ራሱን የሚያቀናበት ደውል ተደውሏል። ለዚህ በአንድነት መነሳት የቅድሚያ ግዴታችን ነው። አጀንዳችን በወልቃይት ተነድፏል። እኛ አማራ ነን! ብሏል። አማራነትን ያነገበው የአማራ ጦር ጎንደር ገብቶ፤ የወልቃይትን አጀንዳ ያነገቡትንና ወኪል ተጠሪ የሆኑትን በሰዓቱ ታድጓቸዋል። በርግጥ ወራሪው ጦር የበለጠ የታጠቀና በጦር ትምህርት የሠለጠነ ነው። ይሄንን ለአማራው ጀግና የሚነግረው አያስፈልግም። በመርዝ ጋዝ ሁሉ የታጠቀውን የፋሽስት ጣሊያን ጦር፤ በባዶ እግሩ የተሰለፈና ጥቂት አሮጌ ጠመንጃዎችና ጀሌ ተሰብስቦ ነው ለሀገሩ ሕይወቱን ገብሮ ሀገራችን ያቆየልን።

አሁን የትግሬዎቹ ወራሪ ጦር አማራንና አማራነትን ለማጥፋት ጎንደር ሰፍሯል። መንግሥታዊ መዋቅሩን በመቆጣጠር የትግሬዎችን ጥቅም ለመጠበቅ በከባድ መሳሪያ የታጀበው ጦር፤ በፌዴራል ስም በአማራው ላይ ዘምቷል። አሁን የያንዳንዳችን አጀንዳ ለዚህ አማራን ለማጥፋት ለተነሳ ጦር፤ በጎንደር ዙሪያ የተነሳውን ተቃውሞ ከጎኑ መቆምና ማገዝ ነው። በቦታው ድርጅታዊ መሪነቱን የሚሠጥ አካል አለ። በቦታው በቆራጥነት ሕይወቱን ለመሥጠት ታጥቆ የተነሳ ክፍል አለ። ይህን መሪነት ተቀብለን፤ ጎድሏል የምንለውን በማሟላት እገዛ ማድረግ የኛ ኃላፊንት ነው። ይህ ብቻ ነው ድርጅታችን።

በመካከላችን እኔ እንዲህ ነኝ! አንቺ እንዲያ ነሽ! ብለን የምንወዳደርበት የቅንጦት ጊዜ የለንም። በውጪ ለምንገኝ አማራዎች በሙሉ፤ ጥያቄው አንድ ነው። ከወገናችን ጎን እንቆማለን ወይንስ አንቆምም? ነው። ሽማግሌዎቻችን ሲገናኙ፤ እኔ ልቅደም እኔ ልቅደም የሚሉት፤ ተጎንብሰው አንዳቸው የሌላቸውን ጉልበት ለመሳም ነበር። በመካከላችን አክብሮትና ቅድሚያን ለሌሎች መሥጠት አስተምረውናል። አሁንም ሌሎችን ምሩት እየተባባልን አክብሮት በመካከላችን እናስቀድም።

ውድ በግንቦት ሰባት በአባልነት የምትገኙ የአማራ ልጆች
ውድ በሁለቱ ኢሕአፓዎች በአባልነት የምትገኙ የአማራ ልጆች
ውድ በሸንጎ ውስጥ የምትገኙ የአማራ ልጆች
ውድ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ የምትገኙ የአማራ ልጆች

ድርጅት የሚመሠረተው፤ በድርጅቱ መርኀ-ግብር የተካተቱትን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ ነው። ያንን ከግብ ለማድረስ፤ በሕይወት መገኘት ቅድሚያ ግዴታ ነው። አማራው የሚጠፋበት ወይንም የሚኖርበት አጣብቂኝ ሰዓት ከፊቱ ተጋርጧል። አሁን ቃል ኪሳን ከገባችሁበት የድርጅታችሁ መርኀ-ግብር ይልቅ፤ የአማራው ሕልውና የላቀ ስፍራ አለውና፤ ለዚህ ተገዙ። በፖለቲካ አመለካከታችሁ ምርጫ ኖሯችሁ፤ ድርጅቶችን አወዳደራችሁና አመዛዝናችሁ የወደዳችሁትን ለመከተል፤ ቅንጦቱ አሁን የለም። የወራሪው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የዘር ፖላቲካ ሥር ሰዶ፤ መሳፋፋት ብቻ ሳይሆን፤ አማራውን ለማጥፋት ሀ ብሎ የተነሳበት ዓላማ፤ አሁን የመጨረሻው ግብግብ ፈጦ ከፊታችን ተጋርጧል። ይህ በአጥር የተለየ ነው። እኔ አጥር ዘልያለሁ። በአጥር ላይ መቆም የለም። እሾሁ ይዋጋል!

ወልቃይት የትግሬዎች መንግሥት መቀበሪያ ነው። ለዚህ የሚደረገው ትግል ቀላል አይደለም። ይህ ትግል ግን ወሳኝ ነው። ሊዳከምና ለበረታ ይችላል። የኛ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው። የትግሬዎች መንግሥት፤ መንግሥታዊ መዋቅሩን በመጠቀምና ዲፕሎማቲካዊ ግንኙነቱን በመሳብ፤ የትግሬዎችን ጥቅም ለማስጠበቅ የማያደርገው የለም። እናም አሁን ባለው አንጻራዊ ጉልበት፤ ብዙ ጉዳት ሊያደርስና ትግሉን ሊያጨልምብን ይችላል። ዋናው ቁምነገር ግን፤ የማይበርደውን ትግል በምንችለው ሁሉ፤ በአንድነት ተነስተን መርዳት ነው። መርፌ እየተወጋች የመከነችው ዘመዳችን፣ ከአዲግራት የተበላሸና መጣል ያለበት ውዳቂ መድሐኒት የተጋተው ዘመዳችን፤ ለትግሬዎችና ለሱዳን የተሠጠው ለሙ መሬታችን፣ ደንበራችን ተገፍቶ መሐከሉ ዳር የሆነበት መኖሪያችን፤ . . . እስከመቼ! እስከመቼ! እስከመቼ!

በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ መንግሥት የለም። የፌዴራልም የሚባል የለም። ያለው የትግሬዎች መንግሥት ነው። መንግሥታዊ መዋቅሩም የሚያገለግለው የትግሬዎችን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው። እብሪቱ ካራሱ በላይ የዘለቀው ይህ የትግሬዎች ጉድን፤ በምንግሥቱ ስም ሳይሆን በአባይ ወልዱ ትዕዛዝ ነው የትግሬ ጦር ተልኮ ጎንደር ገብቶ የወልቃይት ኮሚቴ አባላትን አፍኖ ለመውሰድ የመጣው!

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የትግሬዎች መንግሥት ነው። ይህ የትግሬዎች መንግሥት ሕጋዊ አይደለም። ይህን የትግሬዎች መንግሥትና የትግሬዎች ጦር መዋጋት ትክክለኛና ግዴታ ነው። ለዚህ ደግሞ የተለያዩ ድርጅቶችና የተለያዩ ጦሮች አያስፈልጉንም። ስለዚህ በአንድነት አማራ ነን ብለን እንነሳ!